አንተ ጎዳና ፣ አንተ መንገድ፥
ትንሣኤ ክርስቶስ የሙታን ገድ፥
ጎዳና
መንገድ
‘ማይነሣ የለም ‘ማይቆም ለፍርድ።
መውጊያውን ሰብሮ ሞት ገድሎ ሞቱ፥
ሰይጣን ተማርኮ በ”መኑ ውእቱ”፥
መስተፃርራን ታርቀው ሰባቱ፥
ጥል ተገድሎልን ነፍሳት ሲፈቱ፥
ተንሥአ እሙታን አመ ሠለስቱ።
ያስተሠረየ የዓለምን ኃጢአት፥
የታረደልን ፋሲካ መሥዋዕት፥
የአምደ ሰባቷ የጥበብ ፍሪዳ፥
ሞዐ አንበሳ ዘእም ይሁዳ።
ለአንስት ተገልጦ ታየ ለሐዋርያት፥
በኤማሁስ ፍኖት ጠቅሶ ነቢያት፥
‘ሚሸሽ መልሶ ለመቶ ሃያው፥
“ሰላም ለክሙ” አላቸው ሕያው።
ሆኖ ተነሣ ላንቀላፉት በኩር፥
ተከፈተልን ያ የበጎች በር፥
በሞት ፣ ትንሣኤው ብንተባበር፥
ከድል ነሺዎች አለን መደመር፥
እናየዋለን ሲመጣ በአየር።