የማንን የሙዚቃ ግጥም ማየት ይፈልጋሉ?

ግርማ ተፈራ – ፍቅር በ መጠኑ

በ እውነተኛ ስሜት አስበሽ ለመንፈስ

በመጠኑ አፍቅሪኝ ብዙ ዘመን ድረስ

እፍፍ ያሉት ፍቅር የያዙት ቸኩሎ

በጣም ይግል እና ይጠፋል ተቃጥሎ

ፍቅር የ ሰዉን ልጅ ሲይዝ በ ዝግታ

ጠንካራ ይሆናል በ መላላት ፋንታ

የ ችኮላ ነገር አያስተማምንም

ፍቅሬ ፍቅሬ ሰላልሽ እውነት አይመስለኝም

             ////

መች ወዲያው ይነጋል መቼስ ወዲያው መሽቶ

ሰኔ አይታጨደም ሰኔ ላይ ተዘርቶ

እንዲህ ነው ተፈጥሮ ሂደት አለው ሁሉ

ዘመን እንዲኖረው ይሁን በመጠኑ

ፍቅር በመጠኑ

            ////

እንዳይሰናከል በ አጭሩ

መድረሻው እንዲያምር ጅምሩ

ሰክን ማለት ነው ሚስጥሩ

ተጠብቆ እንዲኖር ዉበቱ

አስደሳች እንዲሆን ስሜቱ

ያስፈልጋል ረጋ ማለቱ

          ////

በ እውነተኛ ስሜት አስበሽ ለመንፈስ

በመጠኑ አፍቅሪኝ ብዙ ዘመን ድረስ

እፍፍ እፍፍ ያሉት ፍቅር የያዙት ቸኩሎ

በጣም ይግል እና ይጠፋል ተቃጥሎ

በጣም ትንሽ ሳይሆን በጣምም ሳይበዛ

ፍቅርን ሲመጥኑት አለው ትልቅ ለዛ

ስልዚህ ውደጂኝ በ እውነተኛ መንፈስ

እንዳትለዋወጪ ብዙ ዘመን ድረስ

         /////

ፍቅር የበዛ እንደሁ ችሎ ይቃጠላል

አውቀው በ መጠኑ ቢያደርጉት ይሻላል

እውነታኛ ስሜት ፈላጊዎች ብትሆኑ

ፍቅር ጠቃሚ ነው ሲሆን በመጠኑ

              /////

እንዳይሰናከል በ አጭሩ

መድረሻው እንዲያመር ጅምሩ

ሰከን ማለት ነው ሚስጥሩ

ተጠብቆ እንዲኖር ዉበቱ

አስደሳች እንዲሆን ስሜቱ

ያስፈልጋል ረጋ ማለቱ

Scroll to Top