የጀማመርኩት የነካካሁት
ከዛሬ ነገ ይሆናል ያልኩት
የጎደለኝም ያለኝም ነገር
ለማመስገንም የሚለኝም ቅር
አቤቤቤቤቤት
ሲነጋ የጨለመ ሌት
ሲፀዳ ያንተም የኔም ቤት
የተሸፈነም ገመና
ይገለጣል ገና
አ ……ብዬ
ብወጋም ችዬ
አቅም እንዳላጣ
ባንቺ ለመጣ
ካቃተኝ መኖር ተፋቅሮ
ሁሌ መባከን ሁሌ እንጉርጉሮ
አትከልክሉኝ ልናገር (x2)
ያንቺም ሀገር ነው የኔ ሀገር (x2)
የተዘረፍኩት ልቤን ነው (x2)
ከፋኝ ሰው ሲለኝ ቀን ጣለው (x2)
ስንቱን ተው ብለሽ ትቻለሁ
ላንቺ ስል ብዙ አጥቻለሁ
እም በከርስደህ
አትበሉኝ ተወው ናቅ አድርገህ
ካጠፋሁ አርሙኝ
አትናገር ግን አትበሉኝ
እም በከርስደህ
አትበሉኝ ተወው ናቅ አርገህ
ዝምማ ዝም ነው
የሚያስታውስህ ሰው ማነው
የጀማመርኩት የነካካሁት
ከዛሬ ነገ ይሆናል ያልኩት
የጎደለኝም ያለኝም ነገር
ለማመስገንም የሚለኝም ቅር
አቤቤቤቤት
መከበር ሆኖ በከንፈር
በሆድ ይፍጀው ነገር ማሰር
እያለ እውነት መናገር
በመሸበት ማደር
አ……ብዬ
ብወጋም ችዬ
ዛሬን ስለፋ
ነገን በተስፋ
ስጨነቅ
ላለመጨነቅ
ብከፋም ሳልርቅ
ላመሌ ስስቅ
አትከልክሉኝ ልናገር
ያንተም ሀገር ነው የኔ ሀገር
ያለመናገር ዝምታ
ልጓም ይሆናል ይሉኝታ
ሁሉንም መቻል ከባድ ነው
መብለጥ መበለጥ ልክ አለው
እም በከርስደህ
አትበሉኝ ተወው ናቅ አርገህ
ካጠፋሁ አርሙኝ
አትናገር ግን አትበሉኝ
እም በከርስደህ
አትበሉኝ ተወው ናቅ አርገህ
ዝምማ ዝም ነው
የሚያስታውስህ ሰው ማነው