የማንን የሙዚቃ ግጥም ማየት ይፈልጋሉ?

ግርማ ተፈራ – ደሞ ሌላ

እስኪ ማን ማን ሊወደድ ካንቺ እኩል ሚዛን ደፍቶ

ሲያዩትም ያላማረ ቢበላም አይጥም ከቶ

ከ ሰው መርጦ ለ ሹመት ከዛፍም ያለው ጥላ

ይባላል ደሞ የለም ተወዳጅ ካንቺ ሌላ

               /////

ደሞ ሌላ አለ ወይ ካንቺ ሌላ

ደሞ ሌላ በ ፍቅር የተሞላ

ደሞ ሌላ አይኔ ቢያይ ሌላ ዉበት

ደሞ ሌላ ልቤማ አንቺ አለሽበት

             ////

ስንት አልፎ ደክሞ ነው ልቤ ልብሽ ጋር የደረሰው

አፈር ዘግኖ ምሏል መቼም ላይለመድ ከ ሌላ ሰው

ሚስጥሩ ምንድነው ብዬ ራሴን ብጠይቀው

መልሱን ይሰጠኛል ፍቅርሽ ውስጤን እስከሚደንቀው

                  /////

እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ

ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ

               /////

ደሞ ሌላ አለ ወይ ካንቺ ሌላ

ደሞ ሌላ በ ፍቅር የተሞላ

ደሞ ሌላ አይኔ ቢያይ ሌላ ዉበት

ደሞ ሌላ ልቤማ አንቺ አለሽበት

             /////

እስኪ ማን ማን ሊወደድ ካንቺ እኩል ሚዛን ደፍቶ

ሲያዩትም ያላማረ ቢበላም አይጥም ከቶ

ከ ሰው መርጦ ለ ሹመት ከዛፍም ያለው ጥላ

ይባላል ደሞ የለም ተወዳጅ ካንቺ ሌላ

 

               /////

ደሞ ሌላ አለ ወይ ካንቺ ሌላ

ደሞ ሌላ በ ፍቅር የተሞላ

ደሞ ሌላ አይኔ ቢያይ ሌላ ዉበት

ደሞ ሌላ ልቤማ አንቺ አለሽበት

                /////

የአሁኑ ደስታዬን ሳስበው ያጓጓኛል የነገው

ካለሽኝ አልሰጋም ውዴ ቢሆንም የፈለገው

እንዲህ ብዬ አላውቅም ለ መጣ ወይ ለሄደው

አልነበረም እና ከልብ እንደ አንቺ የምወደው

                  /////

እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ

ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ

 

               /////

ደሞ ሌላ አለ ወይ ካንቺ ሌላ

ደሞ ሌላ በ ፍቅር የተሞላ

ደሞ ሌላ አይኔ ቢያይ ሌላ ዉበት

ደሞ ሌላ ልቤማ አንቺ አለሽበት

Scroll to Top