በ መልክሽ አይደል ወይ በቁንጀናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሃገር
ግን የት ሃገር ግን የት ሃገር
በ መልክሽ አይደል ወይ በቁንጅናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሃገር
ግን የት ሃገር ግን የት ሃገር
ግን የት ሃገር ግን የት ሃገር
አሳሳቅሽ ያምራል እንዳልጠላው
በ እኔው መቀለድሽ ሆዴን በላው
ልቤ ሲራራልሽ ማን አመነው
ምን ላርግ ሁለመናሽ አሳዛኝ ነው
አኳሃንሽ ከ ሃሳብ መች ይፋቃል
ጥርስሽ አስከፍቶም ይናፈቃል
እየተሳቀብኝ አፈቅራለሁ
ደፍሬ እንዳልነግራት እፈራለሁ
/////
ምነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለ ሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በ ይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
/////
አለሁ ለማለቱ እንዲህ የዘገየሽ
እኔን ማሳበዱ ዪሆን የታየሽ
ልራቅ ከ ቁንጀናሽ ከ ሃሳብ ቢነጥለኝ
ቆሜ አላይም ጨርቄን እስኪያስጥለኝ
/////
ምነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለ ሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በ ይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
////
በ መልክሽ አይደል ወይ በቁንጀናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሃገር
ግን የት ሃገር ግን የት ሃገር
ግን የት ሃገር ግን የት ሃገር
////
አጥቼያለሁ መግቢያ ለመሸሻ
ምንም ሰፍራ አይኖርም አንችን መርሻ
መራቅ እንደማልችል አምኛለሁ
ዞሬ ዞሬ ካንቺ እገኛለሁ
አፋልጌ ሳገኝ ደህና መላ
ስውሰን ይባባል የኔ ገላ
አለው ስሰናዳ የሚያሳሳው
የት ሄጄ ነው ፍቅሬን የምረሳው
/////
ምነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለ ሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በ ይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
/////
አለሁ ለማለቱ እንዲህ የዘገየሽ
እኔን ማሳበዱ ዪሆን የታየሽ
ልራቅ ከ ቁንጀናሽ ከ ሃሳብ ቢነጥለኝ
ቆሜ አላይም ጨርቄን እስኪያስጥለኝ
/////
ምነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለ ሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በ ይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ